Skip to content

ኽምራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ የ“ዲጂታል አማራ” የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ 

ኽምራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ከሰቆጣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለሰራተኞችና ለሰልጣኞች የ“ዲጂታል አማራ” ስልጠና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። መድረኩ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ፣ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ተሳትፎ ለማጠናከርና የዲጂታል ልማትን ለማበረታታት ታልሞ ተዘጋጅቷል።

ስልጠናውን ከሰቆጣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንስትራክተር አቶ አበበ ጌታቸው የሰጡ ሲሆን፣ በዲጂታል ክህሎት ለስራ ፈጠራና ለተቋማት ተወዳዳሪነት ያለውን ጠቀሜታ አብራርተዋል።

በስልጠናው የተካተቱት ዋና ዋና ዘርፎች Content Creation, Graphic Design, Digital Marketing, Web Development እና Network Configuration and Maintenance ናቸው። ተሳታፊዎችም በጥያቄና ውይይት በንቃት ተሳትፈዋል።

የኮሌጁ ዲን ሲ/ር ትግስት መለሰ እንደገለፀችው፣ የዲጂታል አማራ ፕሮግራም የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን፣ የስራ እድልንና ብቁ የሰው ኃይል ልማትን ለማጠናከር ጠቃሚ ሲሆን፣ ስልጠናውም በቀጣይ ዙሮች ለሁሉም ሰልጣኞች እንዲዳረስ ይቀጥላል።

Article topics