በቀን፦ 08/10/2018 ዓ.ም
የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅና ብቁ እና በሥራ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት፣ ኮሌጁ በአብክመ ሥራና ሥልጠና ቢሮ አቅጣጫ መሠረት የስልጠናና የውስጥ ጥራት ቁጥጥር ስራዎችን አካሂዷል። በዕለቱ የኮሌጁ አመራሮች፣ መምህራን፣ የላይብረሪ ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
በስልጠናው የጥራት ማስጠበቅ፣ የዲጂታል ላይብረሪ አጠቃቀምና የኢንስፔክሽን/ሱፐርቪዥን አሰራር ላይ ትኩረት ተደርጓል። ዓላማውም የመማር-ማስተማር ጥራትን፣ የተማሪዎችን ብቃት እና የተቋሙን አፈጻጸም ማሻሻል ነው።
ስልጠናውን በተግባር ለማስተርጎም ሁለት የውስጥ ጥራት ማረጋገጫ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፦
- የትምህርትና ስልጠና ክትትል ኮሚቴ፦ የመማር-ማስተማር ሂደትን፣ የመምህራን አፈጻጸምንና የተማሪዎችን ብቃት ይከታተላል።
- የፊዚካል ፋሲሊቲ፣ መሰረተ-ልማት ግብዓትና ዲጂታል ላይብረሪ ክትትል ኮሚቴ፦ የመማሪያ ክፍሎችን፣ የላብራቶሪ ግብዓቶችን፣ መሰረተ-ልማትንና የዲጂታል ላይብረሪ ዝግጁነትን ይቆጣጠራል።
የክትትል አሰራር፦ ሁለቱም ኮሚቴዎች በተዘጋጀ የክትትል ቼክሊስት መሠረት በየሶስት ወሩ የውስጥ ሱፐርቪዥን በማካሄድ ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በተገኙ ክፍተቶችም የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል።
ማጠቃለያ፦ ይህ እንቅስቃሴ ኽምራ ኮሌጅ በጤናና በቢዝነስ ዘርፎች ጥራት ያለው፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ለሥራ ገበያ ተገቢ የሆነ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ያጠናክራል።
