የኽምራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ክፍል ጋር በመተባበር በኮሌጁ ግቢ ውስጥ የተማሪዎችን የፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ መርሃ-ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተከናወነ በሚገኘው በዚህ የምዝገባ ሂደት፣ የኮሌጁ ሰልጣኞች ለብሄራዊ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን የፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።
በተለይም በአሁኑ ወቅት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉን ለማዘመንና መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ ለመያዝ እየተተገበረ ባለው የEAIMS (Education and Training Management Information System) ሥርዓት ላይ ተማሪዎች በሲስተም ለመመዝገብ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር አስፈላጊ በመሆኑ፣ ኮሌጁ አገልግሎቱን ወደ ግቢው በማምጣት ተማሪዎቹ በተለያዩ የምዝገባ ማዕከላት ያጋጥሟቸው የነበሩትን የእንግልትና የወረፋ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያግዝ አገልግሎት አቅርቧል።
ዲጂታል አገልግሎትን በግቢው በማቅረብ፣ ለተማሪዎች ቀላል፣ ተደራሽና የተሳለጠ አገልግሎት!
