ኽምራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ከጤና ትምህርት ክፍሉ ጋር በመተባበር ለዋግ ስዬም አድማሱ ወሰን እና ለኮሎኔል አማረ ሞላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች የአባላዘር በሽታዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቷል። በዚህ መርሃ ግብር 200 ብሮሸሮች ተዘጋጅተው ለተማሪዎች ተሰራጭተዋል። ትምህርቱም የአባላዘር በሽታዎች ምንነት፣ ዋና ዋና ምልክቶች፣ የመተላለፊያ መንገዶች፣ ሕክምና እና መከላከያ ዘዴዎችን ያካተተ ሲሆን ተማሪዎች ስለ ጤናቸው ተገቢ ግንዛቤ እንዲያገኙ እና ራሳቸውን ከበሽታዎቹ እንዲጠብቁ ለማገዝ ያለመ ነው።
የአባላዘር በሽታዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ
